ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ አቶ አሕመድ ሽዴና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

(ከላይ ከግራ ወደቀኝ) ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ (ከታች ከግራ ወደቀኝ) ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ አቶ አሕመድ ሽዴና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አባላቱ ስድስት ሲሆኑ፣ ሁሉም በሚኒስትር ማዕረግ ያሉ ባለሥልጣናት ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 29, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሔደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ስድስት አባላት ያሉት ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ማቋቋሙን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ከተወያየባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ፤ የኮሮና ቫይረስን ሥርጭት ለመከላከል በሚደረገው ክትትል ጉዳይ ላይ ሲሆን፤ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚመራና ስድስት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ሚኒስትሮችን ያካተተ ኮሚቴ እንዲቋቋም ወስኗል።

ስድስቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ክትትል የሚያደርግ ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ አባላት፤

1. ዶ/ር ሊያ ታደሰ - የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ፣
2. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የሰላም ሚኒስትር፣
3. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ - የገቢዎች ሚኒስትር፣
4. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ - የትራንስፖርት ሚኒስትር፣
5. አቶ አሕመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትርና
6. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መኾናቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ