Bank of Amhara

አማራ ባንክ አክስዮን ማኅበር

የተፈረመ ካፒታሉ 5.3 ቢሊዮን ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉ 4 ቢሊዮን ደርሷል፤ የአክስዮን ሽያጩን ለአምስት ሳምንት አራዝሟል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ አማራ ባንክ አክስዮን ማኅበር ባላፉት ስምንት ወሮች አክስዮን የገዙ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ቁጥር 145 ሺህ መድረሱንና ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈል ካፒታል ማሰባሰቡን ገለጸ።

ባንኩ ለተጭማሪ አምስት ሳምንት የአክስዮን ሽያጩን ማራዘሙን ለማስታወቅ ዛሬ በሠጠው መግለጫ፤ የተፈረመ ካፒታሉ ከ5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታውቋል።

ባንኩ አሁን የደረሰበት የተከፈለ ካፒታልም ኾነ የተፈረመ ካፒታል፤ በአገሪቱ የግል ባንክ መመሥረታ ወቅት የተመዘገበ ከፍተኛ መጠን ያለው ኾኗል።

ይህ ብቻ ሳይኾን፤ በአሁኑ ወቅት የባንኩ ባለአክስዮን ለመኾን የባንኩ አክስዮኖችን የገዙት ከ145 ሺህ በላይ መድረሱ መጠቀሱ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ባለአክስዮኖች የያዘ ባንክ አድርጎታል።

ባንኩ አክስዮን ሽያጩን ያራዘመው በአዲሱ የብሔራዊ ባንክ ሕግ መሠረት የውጭ ዜግነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን አክስዮን ለመሸጥ አስቦ ነው ተብሏል። ባንኩ ከዚህ ቀደም የአክስዮን ሽያጩ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚያበቃ አስታውቆ ነበር። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ