በመላ አገሪቱ ትምህርት ቤቶች ለ15 ቀናት ይዘጋሉ

በመላ አገሪቱ ትምህርት ቤቶች ለ15 ቀናት ይዘጋሉ

ትላልቅ ስብሰባዎችና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ለ15 ቀን አይካሔዱም

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 16, 2020)፦ ከዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በመላው አገሪቱ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ተገለጸ። በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አምስተኛ ሰው ተገኝቷል።

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባሉበት ኾነው አስፈላጊ ክትትል ይደረግላቸዋል በማለት ገልጸዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከተወሰነው ከዚህ ውሳኔ ጎን ለጎን፤ የሃይማኖት ተቋማትም ምዕመናን የሚሰበሰቡባቸውን ሁኔታዎች በጥንቃቄ ይመለከቱ ዘንድም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቫይረሱ የተያዘ አምስተኛ ሰው ተገኝቷል። ይህ ግለሰብ ከዱባይ የመጣ መኾኑ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ