በኮሮና ምክንያት ምርጫ ቦርድ ሠራተኞቹ ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ወሰነ

በኮሮና ምክንያት ምርጫ ቦርድ ሠራተኞቹ ወደ ቢሮ እንዳይገቡ ወሰነ

ከቦርዱ ጋር የሚሠራ አንድ የውጭ አገር ዜጋ የኮሮና ምልክቶች ታይተውበታል

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 16, 2020)፦ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ፤ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠራተኞቹ ከቤታቸው ኾነው ሥራ እንዲሠሩ ቦርዱ መወሰኑን ገልጿል።

ቦርዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበት ምክንያት፤ ከአንድ ወር በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባ አንድ የውጭ አገር ዜጋ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ስለታዩበት እንደኾነ ገልጿል። ግለሰቡ ለቦርዱ ቴክኒካዊ ድጋፍ የሚሠጥ ባለሙያ መኾኑም ታውቋል።

ቦርዱ ለግለሰቡ ምርመራ እንዲካሔድ የጠየቀ ሲሆን፤ የምርመራ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ የቦርዱ ሠራተኞች በየቤታቸው ኾነው መደበኛ ሥራቸውን እንዲሠሩ ተወስኗል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ