ዶክተር ቶላ በሪሶ

ዶክተር ቶላ በሪሶ፤ የኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

ዶክተሩ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 17, 2020)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው፤ በለይቶ ማቆያ ለብቻቸው ተቀምጠው የነበሩት የኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ፤ ከቫይረሱ ነፃ መኾናቸው ታወቀ።

ከእርሳቸው ሌላ ከ12 ቀናት በፊት ከጃፓናዊው ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 21 ሰዎችም ከቫይረሱ ነፃ መኾናቸው ተገልጿል።

ዶ/ር ቶላ በሪሶ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በመኾናቸው ጋር ተያይዞ ከጃፓናዊው ሰው በትምህርት ዘርፍ በጎ አድራጎት የሚሠራ በመኾኑ ነበር ግንኙነቱ ተፈጥሮ የነበረ መኾኑን መዘገባችን አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ