Mr. Tewolde GebreMariam was appointed as Group Chief Executive Officer of Ethiopian Airlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያ

አየር መንገዱ በአራት ወር 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል፤ የሚቀነስ ሠራተኛ የለም ብሏል

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 7, 2020)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ገለጹ።

አሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ መጠቃታቸው ሪፖርት ከተደረጉት ሰዎች መካከል፤ ሦስቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሠራተኞች መኾናቸውን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት አራት ወራት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተፈጠረ የገበያ እጦት፤ አየር መንገዱ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ እንደገባ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. አቶ ተወልደ ከሠጡት መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

ባለፉት አራት ወራትም አየር መንገዱ በአስር ከመቶ አቅሙ ብቻ እየሠራ በመኾኑ፤ በተጠቀሱት ወራት ውስጥ ብቻ 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል።

በዛሬው የዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለጻ፤ አየር መንገዱ ቋሚ ሠራተኞቹን ይዞ ለመቀጠል መወሰኑንና አንድም ቋሚ ሠራተኛ እንደማይቀነስ አስታውቀዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ