PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ሲቪክ ማኅበራትም በውይይቱ ተሳትፈዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 29, 2020)፦ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የተራዘመውን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫን (ምርጫ 2012) ለማካሔድ አስቸጋሪ በመኾኑ፤ መንግሥት አራት የመፍትሔ ሐሳቦችን በማቅረብ ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት ጋር ውይይት በማካሔድ ላይ ነው።

“ኮቪድ 19 ምርጫን ማራዘምና የሕግ አማራጮች” በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሚመራው የውይይት መድረክ ላይ ከመንግሥት የቀረቡት አራቱ አማራጮች፤

አማራጭ አንድ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣
አማራጭ ሁለት፦ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፤
አማራጭ ሦስት፦ ሕገ መንግሥት ማሻሻል እና
አማራጭ አራት፦ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ መኾናቸው ተጠቅሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ