እኅተ ማርያም

እኅተ ማርያም (ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ)

60 ደላሎች ታስረዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 29, 2020)፦ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራስዋን “ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ” የሚል መጠሪያ በመስጠት ስትንቀሳቀስ የቆየችው እኅተ ማርያም በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ግለሰብ ዛሬ ከመሸ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች።

አነጋጋሪ መልእክቶችንና ስብከቶችን ስታካሒድ የቆየቸው እኅተ ማርያም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በሚጻረር መንገድ በእምነት ስም እስከ አንድ መቶ የሚደርሱ ተከታዮችን ሰብሰባ በመገኘቷ መኾኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ማምሻውን፤ ረቡዕ ሚያዝያ 21 ቀን አስታውቋል ተብሏል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና ሥርጭቱን ለመቀነስ በወጣው አዋጅ፤ ከአራት ሰው በላይ መሰብሰብ የተከለከለ ቢሆንም፤ ግለሰብዋ ይህንን በመጻረርዋ በቁጥጥር ስር መዋልዋ ታውቋል።

ይኸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ጨምሮ እንደገለጸው፤ ግለሰብዋ ዛሬ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ጉዳይ በተጨማሪ በሌሎች ወንጀሎችም በግለሰብዋ ላይ ሰፊ ምርመራ እንደሚያካሒድ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን ማስታወቁን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በእህል በረንዳ አካባቢ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጻረር የድለላ ሥራ ለመሥራት ነው በሚል 60 ሰዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው በመገኘታቸው፤ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ተገልጿል። (ኢዛ)

የአዲስ ከተማ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ያዋላቸው እነዚህ ግለሰቦች እንዲህ ባለመልኩ እንዳይሰበሰቡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም ተግባራዊ ባለማድረጋቸው፤ ዛሬ በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ