“የህዳሴ ግድቡን ጨርሰናል፤ ውኃ መሙላት ይጀመራል” ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ
 
		የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለውኃ ሙሌት ዝግጁ ኾነ
አስራ አንድ ታዛቢዎች የሚገኙ ሲሆን፤ ደቡብ ሱዳን፣ ማሊ፣ ኮንጎና ኬንያ ይገኙበታል
ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 5, 2020)፦ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ውኃ ለመሙላት የሚያስችላትን ግንባታ መጨረስዋንና የውኃ መሙላት ሒደቱን እንደምትጀምር የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
ዛሬ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በሰጡት መግለጫ፤ የግድቡን ውኃ ለመሙላት የሚያስፈልገው የግንባታ ሒደት ማለቁን ከማስታወቃቸውም በላይ፤ ከዚህ ቀጥሎ ወደ ውኃ ሙሌቱ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
በተፋሰሱ ሦስት አገራት ማለትም በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መኻል ሲደረግ የነበረው ውይይት ተቋርጦ የነበረ በኾንም፤ በቅርቡ እንደሚጀመር ታውቋል። ድርድሩን የአፍሪካ ሕብረት የሚመራው ሲሆን፤ 11 ታዛቢዎች እንደሚኖሩና፤ ከእነዚህም ውስጥ ደቡብ ሱዳን፣ ማሊ፣ ኮንጎና ኬንያ እንደሚገኙበት ተገልጿል። (ኢዛ)



