Wolaita

ወላይታ

እንዲቀቁ መደረጉ በዞኑ ያለውን አለመረጋጋት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 13, 2020)፦ ከሁለት ቀን በፊት ተይዘው በእስር ላይ የነበሩት የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፤ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ።

ከእነዚህ የዞኑ አመራሮች እስር ጋር ተያይዞ በዞኑ በተፈጠረ አለመረጋጋት የሰው ሕይወት መጥፋቱና ለአካል መጉደል ምክንያት ኾኗል።

ዛሬ ሐሙስ ነኀሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በአንጻራዊነት ዞኑ የተረጋጋ ነበር የተባለ ሲሆን፤ ያለመረጋጋቱ በነበረበት ወቅት የጸጥታ ኃይሉ ያልተመጣጠን ኃይል ተጠቅሟል የሚል አስተያየት ሲሰነዘር ነበር።

የዞኑ አመራሮች ዛሬ በዋስ እንዲለቀቁ መደረጉ በዞኑ ያለውን አለመረጋጋት ያረግባል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ