Prof. Mesfin WoldeMariam

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በፊት የሻማ ማብራትና የሽኝት ፕሮግራም ይካሔዳል

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 5, 2020)፦ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።

የቀብር ሥርዓቱን ለማስፈጸም የተቋቋመው ኮሚቴ እንዳስታወቀው፤ ነገ የቀብር ሥርዓቱ ከመፈጸሙ በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልደት አዳራሽ የሽኝት ፕሮግራም ይካሔዳል።

ዛሬ ምሽት ላይ ደግሞ በመኖሪያ ቤታቸው የሻማ ማብራት ፕሮግራም እንደሚኖርም ተጠቅሷል።

የልደት አዳራሹ ፕሮግራም ልጆቻቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሚፈጸም እንደሚኾን ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ