Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Gedu Andargachew (R) and US ambassador in Ethiopia H.E. Michael Raynor (L), February 13, 2020. (Photo: The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው (በቀኝ) እና አምባሳደር ማይክ ሬይነር (በግራ)፤ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. (ፎቶ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ጦርነት ቀስቃሽ መኾኑን አሳወቁ

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 24, 2020)፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግብጽ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች በሚል የተናገሩትን አወዛጋቢ ንግግር አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አዲስ አበባ የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠየቀ።

አቶ ገዱ አምባሳደር ማይክ ሬይነርን በጽሕፈት ቤታቸው አስጠርተው፤ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ አድርገዋል።

በአምባሳደሩ በትራምፕ ንግግር ላይ ስለሰጡት ማብራሪያ የተገለጸ ነገር ባይኖርም። አቶ ገዱ ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሦስቱ የተፋሰሱ አገሮች ድርድር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የተሳሳተ መኾኑንና በድርድሩ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥር ስለመኾኑ ለአምባሳደሩ አስረድተዋል።

ንግግሩ አሜሪካንን እየመራ ካለ ኃላፊነት ከሚሰማው ፕሬዝዳንት የማይጠበቅ፣ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ጦርነት ቀስቃሽ መኾኑን በመግለጽ ጭምር የትራምፕ ንግግር ትክክል ያለመኾኑን አስረድተዋል ተብሏል።

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት እና አጋርነት የማያንጸባርቅ፤ እንዲሁም በየትኛውም የዓለም አቀፍ ሕግ ተቀባይነት የሌለው ንግግር ነው ብለውታል።

አቶ ገዱ አምባሳደሩን አስጠርተው የአገራቸውን አቋም ባንጸባረቁበት በዚህ ቆይታቸው፤ ኢትዮጵያ በሉዓላዊነቷ ላይ የሚሰነዘሩ የየትኛውም አገር ዛቻዎች እንደማትንበረከክ ለአምባሳደሩ ገልጸው፤ ወደፊትም ትራምፕ እንደተናገሩት ዐይነት ንግግሮች ተቀባይነት የማይኖራቸው መኾኑን መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ