ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀንሰው የነበሩ ሦስት ጄኔራሎች ወደ ሠራዊቱ እንዲመለሱ አዘዙ

ጄኔራሎች ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ (በግራ) እና ሌ/ጄ አበባው ታደሰ (በቀኝ)
ሦስቱ ጄኔራሎች ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሌ/ጄ ዮሐንስ ገብረመስቀል እና ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ናቸው
ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 4, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩትን ሦስት ጄኔራሎች ወደ መከላከያ ሠራዊት እንዲመለሱ ትእዛዝ ሰጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡላቸው ሦስት ጄኔራሎች ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሌ/ጄ ዮሐንስ ገብረመስቀል እና ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ናቸው።
እነዚህ ጄኔራሎች ከለውጡ በፊት ከሠራዊቱ ያለአግባብ እንዲቀነሱ ተደርገው የነበሩ መኾኑ ይታወቃል። (ኢዛ)