መንግሥት ለትግራይ ክልል ልዩ ኃይል ጥሪ አቀረበ
ሕወሓት
ሙሉና አስተማማኝ ዋስትና እሰጣለሁ ብሏል
ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 4, 2020)፦ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መንግሥት አሁን ባወጣው መግለጫ፤ ተገድደውና ሳይፈልጉ ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በሰላማዊ መንገድ ወደ አጎራባች ክልሎችና በአቅራቢያቸው ወደአለው የመከላከያ ሠራዊት ከገቡ ሙሉና አስተማማኝ ዋስትና እንደሚሰጣቸው አስታወቀ። (ኢዛ)



