ሁለት የኤፈርት ሕንጻዎች በጸጥታ ኃይሉ ተከቧል
በሕወሓት ኤፈርት ድርጅት ከሚተዳደሩት ጥቂቱ ድርጅቶች
ማንም መግባትና መውጣት እንዳይችል ተከልክሏል
ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ አዲስ አበባ በቦሌ መንገድ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ የሚገኘው የሱር ኮንስትራክሽን ዋና መሥሪያ ቤትና ሜጋ ሕንጻ በመባል የሚታወቁት በኤፈርት ባለቤትነት የሚተዳደሩት ሁለቱ ሕንጻዎች በአሁኑ ወቅት በጸጥታ ኃይሎች መከበባቸው ተገለጸ።
ወደ ሁለቱም ሕንጻዎች መግባትና መውጣት የተከለከለ ሲሆን፤ የጸጥታ ኃይሉ በሕንጻዎቹ ፍተሻ ሊያደርግ ስለመኾኑ ተገምቷል። ኤፈርትን ሕወሓት እንደሚያስተዳድረው ይታወቃል። (ኢዛ)



