ሕገወጥ የጦር መሣሪዎያዎች

ለጥፋት ተልዕኮ በሕወሓት ተዘጋጅተው የነበሩና በቁጥጥር ሥር የዋሉት የጦር መሣሪያዎች

162 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል
ከሱዳን በገዳሪፍ በኩል ሊገባ የነበረ 95 ሺህ ጥይት ከነግለሰቦቹ ተያዘ

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕወሓት ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው የጦር መሣሪዎያዎችና ተልዕኮውን ለማስፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት (እሁድ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም.) ብቻ በአዲስ አበባ ከ355 በላይ የጦር መሣሪያዎች ተይዘዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው፤ “የሕወሓት የጥፋት ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮው ያዘጋጃቸው የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል” ብሎ፤ መዲናዋን ለማወክ ቡድኑ ያዘጋጃቸው ከ355 በላይ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ከ14 ሺህ በላይ ጥይቶች ጋር በቁጥጥር ሥር ውሏል።

የጥፋት አጀንዳውን ለማስፈጸም የተጠረጠሩ 162 ግለሰቦችንም መያዙን የሚያመለክተው የፖሊስ መረጃ፤ ተጠርጣሪዎቹ ምርመራ እየተደረገባቸው መኾኑንም አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና በሱዳን በኩል በገዳሪፍ ግዛት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረውን 95 ሺህ ጥይት የሱዳን ጦር መያዙ ታውቋል። ሱዳን ትሪቢዩን የሱዳን ጦር ወታደራዊ ደኅንነትን ጠቅሶ እንደዘገበው ከኾነ፤ በሕገወጥ መንገድ ሊገባ የነበረውን ጥይትና አደንዛዥ እጽ መቆጣጠር ከመቻሉም በላይ ድርጊቱን ሊፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቁል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ