በአዲስ አበባ ወድቆ ያገኙት ቦምብ የፈነዳባቸው አምስት ሕፃናት ተጎዱ

በቦምብ ፍንዳታው እጁ ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰበት የ13 ሕፃን
የ13 ዓመቱ ሕፃን በእጁ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 14, 2020)፦ በአዲስ አበባ ወድቆ ያገኙትን ቦምብ እጃቸው ላይ የፈነዳባቸው ሕፃናት ጉዳት ደረሰባቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማምሻውን እንዳስታወቀው፤ ድርጊቱ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባትብ በተለምዶ 02 ወይም ካፕቴን ደምሴ ሰፈር በሚባለው አካባቢ እንደኾነ አስታውቋል።
“ሕግን ለማስከበር እየተሠራ ባለው ሥራ የተደናገጡ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ተላላኪዎች ኾን ብለው ሰዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ልዩ ልዩ ጦር መሣሪያዎችን በየቦታው እየጣሉ ስለኾነ፤ ሕብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ መልእክቱን በድጋሚ ያስተላልፋል” ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ዛሬ ጉዳት የደረሰባቸው እነዚህ ሕፃናት አምስት ሲሆኑ፤ አራቱ ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው፤ አንዱ ግን በእጅ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል። ይህ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የ13 ዓመት ሕፃን ነው። (ኢዛ)