በአምቦ ለብልጽግናና ለዶክተር ዐቢይ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በከፊል

በአምቦ ለብልጽግናና ለዶክተር ዐቢይ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በከፊል

ከ20 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 23, 2020)፦ ዛሬ ጠዋት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ በአምቦ በተካሔደው ትዕይንተ ሕዝብ መሐል ቦምብ ተውርውሮ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።

በድጋፍ ሰልፈኞቹ ላይ የተወረወርው ቦንብ ከ20 በላይ በሚኾኑት ላይ ጉዳይ መድረሱ ታውቋል።

የአምቦ ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፉን ያደረጉት በፈረሰኞች ጭምር ታጅቦ ነበር።

በተወረወረው ቦምብ ከተጎዱት ውስጥ አብዛኛው ፈረሰኞች ናቸው ተብሏል። አንዳንድ መረጃዎች የቆሰሉትን እስከ 29 አድርሰውታል። እስካሁን በጥቃቱ ሕይወቱ ያለፈ ባይኖርም ከተጎዱ ሰልፈኞች ውስጥ አንዳንዶቹ የሕክምና እርዳታ አግኝተው የወጡ ሲሆን፣ የጉዳት መጠናቸው በሕክምና ማዕከል ያቆያቸው እንዳሉም ተጠቅሷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ