በመጨረሻም የጁንታው ሕወሓት የገንዘብ ምንጮች ደረቁ
ኤፈርት
ከ60 ቢሊዮብ ብር በላይ ካፒታል ያላቸው የሕወሓት ኩባንያዎች አካውንት ታገደ
ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 17, 2020)፦ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በሰፊው እጃቸውን አስገብተው ሲንቀሳቀሱ የቆዩና ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዳላቸው የሚታመኑት 34 የሕወሓት ኩባንያዎች የባንክ አካውንት ታገደ። የጁንታው ሕወሓት ቡድን የገንዘብ ምንጮች በስተመጨረሻ ደረቁ።
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ከታገዱት የኤፈርት ኩባንያዎች ውስጥ ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንጂንየሪንግ፣ ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ፣ ኤፈርት ኤሌከትሪካል ቢዝነስ፣ ሼባ ቆዳ ፋብሪካ፣ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ፣ መሶበ ሲሚንቶ ፋብሪካ እና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል ተብሏል።
እነዚህ ኩባንያዎች በሁሉም የአገሪቱ ባንኮች ያላቸው የሒሳብ አካውንትት እንዲታገድ ዓቃቤ ሕግ ያሳወቀ ሲሆን፤ በሕግ ተጠያቂ እንደሚኾኑም ታውቋል። (ኢዛ)



