Ahmed Shide, Minster of Finance

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ

780 ቢሊዮን ብር እዳ አለባቸው

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 15, 2021)፦ በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች ከ780 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ያለባቸው መኾኑ ተገለጸ።

በእዳ ተዘፍቀዋል ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ሜቴክ)፣ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የስኳር ኮርፖሬሽን በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ተብሏል።

እነዚህ ኩባንያዎች በእዳ መዘፈቃቸው መንግሥት ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ብሎ በመለየት የአገር በቀሉ የኢኮኖሚ እቅድ ሪፎርም ውስጥ እንዲካተቱ ተደርገዋል።

ባለፉት 15 ዓመታት ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ሲከናወኑ የነበረ ሲሆን፤ አብዛኞቹ ኢንቨስትመንቶች ደግሞ በመንግሥት በጀት ይከናወኑ የነበረ ሲሆን፤ ይህም ከአገር ውስጥ አና ከውጭ በተገኘ ብድር እንደኾነ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ገልጸዋል። በተለይ ከአገር ውስጥ አበዳሪ ተቋማት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋነኛ በመኾኑ፤ የተቋሙ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ ታምኗ። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ