የማነ ንጉሥ ተገደሉ
አቶ የማነ ንጉሥ
አብረዋቸው ሁለት የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል
ኢዛ (እሁድ የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 21, 2021)፦ ሕወሓትን በመቃወም የሚታወቁትና “ፈንቅል” በመባል የሚታወቀውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሊቀመንበርነት በመምራት የሚታወቁት የማነ ንጉሥ የተገደሉት ከመቀሌ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሔዋኔ ከተማ ነው።
ግድያው የተፈጸመባቸው በጁንታው ርዝራዦች ስለመኾኑ የሚጠቅሱት መረጃዎች፤ አቶ የማነ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ከወደቀ በኋላ ለትግራይ ሕዝብ የሰብአዊ ዕርዳታ በማቅረብ እያገለገሉ ነበር። በተገደሉበት ዕለትም በዚሁ ሰብአዊ ዕርዳታ ላይ እንደነበሩ ታውቋል።
የሕውሓት ጁንታ ቡድን በመታገል ከሚታወቁት አክቲቭስቶች መካከል አንዱ የነበረት አቶ የማነ፤ በጁንታው ርዝራዦች በተገደሉበት ወቅት አብረዋቸው የነበሩ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸውም ታውቋል። (ኢዛ)



