አብን እና ባልደራስ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ)
በምርጫ 2013 የመራጮችን የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት በማሰብ የተመሠረተ የፖለቲካ ትብብር ነው
ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 18, 2021)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ለምርጫ 2013 በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በማድረግ ተፈራረሙ።
ሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነታቸውን አስመልክቶ ዛሬ (ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም.) በሰጡት የጋራ መግለጫ፤ በመጪው አገራዊ ምርጫ 2013 የመራጮችን የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት በማሰብ የተመሠረተ የፖለቲካ ትብብር ነው።
ሁለቱ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ በየግላቸው ለመወዳደር የተመዘገቡ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ጊዜያዊ መረጃ መሠረት፤ አብን 491 እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ ባልደራስ ደግሞ 160 እጩዎችን በማስመዝገብ በምርጫው ይወዳደራሉ።
በዛሬው የሁለቱ ፓርቲዎች የጋራ መግለጫ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የፓርቲዎቻቸውን አቋም የሚያንጸባርቁ መረጃዎች ሰጥተዋል። (ኢዛ)