አቶ ጌታቸው አሰፋ

አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ በመንግሥት የእስር ትእዛዝ ወጥቶባቸው ሲፈለጉ የነበሩት የሕወሓት አመራር እና የቀድሞው የመረጃና ድኅንነት ዋና ዳይሬክተር

አሟሟታቸው በሕመም ነው ተብሏል

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 18, 2021)፦ ከለውጡ በኋላ በብርቱ ሲፈለጉ የነበሩት የቀድሞው ድኅንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ መሞታቸው ተገለጸ።

ኢሳት የመከላከያ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሞቱት በሕመም ነው።

በመንግሥት የእስር ትእዛዝ ወጥቶባቸው ሲፈለጉ የነበሩት የሕወሓት አመራር እና የቀድሞው የመረጃና ድኅንነት ዋና ዳይሬክተር ሉኪያ በተባለ አካባቢ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ፍትሃት ተደርጎላቸው፤ የቀብር ሥርዓታቸው ስለመፈጸሙ ይኸው መረጃ ያመለክታል።

ብርቱ የልብ ሕመም እንደነበረባቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ከቆላ ተንቤን ጀምሮ በቃሬዛ ሲጓጓዙ እንደነበር ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ