በትግራይ ተፈጽሟል በተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ኢሰመኮ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጋራ ለመመርመር ተስማሙ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን (Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights - OHCHR)
ምርመራቸውን በአጭር ጊዜ ለመጀመር ወስነዋል
ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 25, 2021)፦ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን (Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights - OHCHR)፤ በትግራይ ክልል ተፈጽሟል የተባለውን የመብት ጥሰት በጋራ ለመመርመር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሁለቱ ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
ምርመራውንም በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጀመር ከስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው የጋራ መግለጫቸው አመላክቶ፤ ለመነሻም በሦስት ወር እንዲካሔድ መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል። (ኢዛ)



