መድረክ ውርስ ይገባኛል ሲል ኢህአዲግ አፈገፈገ

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. January 15, 2010)፦ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል “ምርጫና ሰብዓዊ መብቶች” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የመጀመሪያውን የፓርቲዎች ክርክር ጀመረ።

 

በክርክሩ ላይ መድረክ ሲያሳውቅ የኢህአዲጉ ተከራካሪ አቶ ሴኮ ቱሬ መድረክ ጠፍቶ ሊያጠፋን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

 

የሀገር ሀብት ኢህአዲግ ብቻውን መጠቀም የለበትም፤ መድረክ የሀገር ሀብት በሙሉ መጋራት አለበት ያሉት የመድረክ ተወካይ አቶ ወንድሙ ኢብሳ፤ ከባንክ ጀምሮ እስከ ታንክ ያሉት መድረክ ድርሻ ሊኖረው ይገባል ብለዋል። በመድረክ ጥያቄ የደነገጡት የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ሴኮ ቱሬ መድረክ አደገኛ አካሄድ መከተሉንና ይህ አካሄዱ “ራሳቸውን አጥፍተው እኛንም ይዘውን እንዳይሄዱ ያሰጋል” ብለዋል።

 

የኢህአዲጉ አቶ ሴኩ ቱሬ የንግግር ብቃት እንደሌላቸው ያስመሰከሩበት ይህ ክርክር፤ ኢህአዲግን ስጋት ላይ የሚጥለው የተከራካሪዎቹ የንግግር ችሎታ ደካማነት እየታየ መሆኑን ታዛቢዎች የገለጹ ሲሆን፤ ከወዲሁ በተነሱ ሃሳቦች ላይ ከመነጋገር ይልቅ ያለፈውን ሁኔታ በማንሳት የማሸማቀቅ ሥራ መሥራትን ኢህአዲግ እንደስልት ተጠቅሞበታል፤ ይህ አካሄድ እስከ ምርጫው ዋዜማ ከቀጠለ ለትችት የሚጋለጠው ፓርቲ ከወዲሁ ይለያል ማለት ነው በማለት ታዛቢዎች አስተያየታቸውን አክለው ገልጸዋል።

 

መድረክ በክርክሩ የኦፍዲኑን አቶ ገበየሁ አያቶንና የሕብረቱን አቶ ወንድሙ ኢብሳን ያቀረበ ሲሆን፤ አቶ ገበየሁ - መንግሥት ሥልጣን ሊያጋራ ይገባል የሚለውን የመድረክን አቋም አንጸባርቀዋል። ኢህአዲግ ሥልጣን ማጋራት “የሕልም እንጀራ ነው” እያለ መሳለቁ ይታወቃል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ