Robel TeklemariamEthiopia Zare (ሐሙስ ጥር 20 ቀን 2002 ዓ.ም. January 28, 2010)፦ በክረምት ኦሎምፒክ ታሪክ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር የመጀመሪያው የሆነው የ35 ዓመቱ ወጣት ሮቤል ተክለማርያም በሚቀጥለው ወር በቫንኩቨር - ካናዳ በሚጀመረው የክረምት (ዊንተር) ኦሎምፒክ ለመሳተፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ።

 

Robel Teklemariam, Torino, Italy 2006ሮቤል ተክለማርያም ከልጅነቱ ጀምሮ በስኪንግ ውድድር (በበረዶ ላይ መንሸራተት ውድድር) ለመሳተፍ የነበረውን ከፍተኛ ምኞት በ31 ዓመቱ በ2006 እ.ኤ.አ. በቶሪኖ ጣሊያን በተካሄደው የዊንተር ኦሎምፒክ ላይ በመሳተፍ እውን ያደረገ የመጀመሪያውና ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው። በቶሪኖው የክረምት ኦሎምፒክ ያመጣው ምኞት አመርቂ ባይሆንም ተስፋ ሳይቆርጥና ልምምዱን በማጠናከር በዚህ በያዝነው 2010 እ.ኤ.አ. በቫንኩቨሩ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክሎ በመሳተፍ ሀገሩን ለሁለተኛ ጊዜ የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ ከማድረግ አልፎ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ የሀገሩን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ ቆርጦ መነሳቱን ለማወቅ ችለናል።

 

ወጣት ሮቤልን በቫንኩቨር የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲና የሀገር ፍቅር ተወዛዋዥ በነበረችው ዝነኛዋ ሙሉ ንጉሴ እየሠለጠኑ ባህላቸውን በማስተዋወቅ ላይ በሚገኙት ታዳጊ ወጣቶች የተቋቋመውና በሙዚቃ፣ በድራማና በባህላዊ ውዝዋዜ ሥራቸው በአጭር ጊዜ ብዙ አድናቂዎችን በማግኘት ላይ የሚገኙት የውቢት ኢትዮጵያ የባህል ክለብ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉለት ታውቋል።

 

ሮቤል የመጀመሪያው የሀገር አቀፍ የስኪንግ ፌደሬሽን ሊቀመንበር ሲሆን፣ ለዊንተሩ ኦሎምፒክ ውድድር በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ ወጣቶችን በምነሳሳትና በማሠልጠን የተሳታፊዎችን ብዛት ለመጨመር እንደሚሠራና ህልሙ ግቡን እስኪመታ እንደሚገፋበት ገልጿል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ