Indira Gandhi international airport arrivals

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ አንዲት ኢትዮጵያዊት ስምንት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሩፒስ (የሕንድ ገንዘብ) የሚያውጣ ሦስት ኪሎ ወርቅ ይዛ በኢንድራ ጋንዲ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በኩል ስትገባ የሕንድ ጉምሩክ ባለሥልጣን በቁጥጥር ስር አዋላት። ኢትዮጵያዊቷ በእጅዋ ላይ አስር ሺህ የአሜሪካ ዶላር እና ስድሳ ሺህ ሩፒስ ተይዞባታል። ግለሰብዋ በወርቅ ኮንትሮባንድ በሕንድ ፖሊስ ስትያዝ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው።

በኢትዮጵያዊቷ እጅ ላይ ረቡዕ ጠዋት የተገኘው ስድሳ ሺህ ሩፒ የባለአንድ ሺህ ኖቶች መሆናቸውን ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል። በሴትዮዋ እጅ ላይ የተገኘው ሦስት ኪሎ ወርቅ ሲሆን፣ ሕንድ ውስጥ ሲሸጥ በአሜሪካ ዶላር ቢያንስ ፻፴፩ (131) ሺህ እንደሚያወጣ ዘገባው ያስረዳል።

ኢትዮጵያዊትዋ ከሁለት ወር በፊትም በወርቅ ኮንትሮባንድ ተይዛ በዋስ መፈታትዋ ታውቋል። በወቅቱ ስድስት መቶ ሃምሳ ግራም ወርቅ በጅዋ ላይ ተይዞ ነበር። ኢትዮጵያዊቷ ሁለት ጊዜም ኢንድራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትያዝ የተነሳችው ከአዲስ አበባ መሆኑ ታውቋል።

በግለስብዋ እጅ ላይ የተገኙት ወርቆችና ገንዘቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የሕንድ ጉምሩክ ፖሊስ ከዚህ የወርቅ ኮንትሮባንድ መደጋገም ጋር በተያያዘ በዚህ የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ራሱን የቻለ የተጠናከረ ቡድን ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለው ታውቋል። ኢትዮጵያዊትዋ ለፖሊስ በተደጋጋሚ እሷ አመላላሽ እንሆነች እንደተናገረች ለመረዳት ተችሏል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ