Prof. Mesfin & Ato Asrat arrival at Bole Ariport, 20080821

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነኀሴ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. August 21, 2008)፦ በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የአንድነት ለዴሞክራሰና ለፍትህ ፓርቲን ዓላማ ለኢትዮጵያኖች ሲያስረዱና ከህዝብ ጋር ውይይት ሲያካሂዱ የነበሩት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም እና አቶ አስራት ጣሴ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸውን ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ አስረዳ።

 

ዛሬ ማምሻውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ ወደ ሃያ የሚሆኑ ሰዎች አቶ አስራት ጣሴን እና ፕ/ር መስፍንን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል።

 

አቶ አስራት ጣሴ የአንድነት ፓርቲ መስራች እና የፓርቲው ዋና ፀሐፊ ሲሆኑ፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ደግሞ የአንድነት ፓርቲ መሥራች እና የፓርቲው ም/ቤት አባል መሆናቸው ይታወቃል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ