የሲዳማ ጉዳይ ነገ ይለያል
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የምርጫው ምልክቶች
ለምርጫው 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል
ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 19, 2019)፦ ለዓመታት የቆየውን የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን እልባት ለመሥጠትና ሲዳማ በክልልነት ይደራጅ፣ ወይም ሲዳማ የደቡብ ክልል ኾኖ እንዲቆይ እፈልጋለሁ የሚለውን ለመለየት ሲጠበቅ የነበረው ምርጫ ነገ ይካሔዳል። ለምርጫው 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል።
ነገ ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሚካሔደው ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ የኾኑ ዝግጅቶችን ያጠናቀቀ መኾኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ ለዚህ ምርጫ በመራጭነት የተመዘጉ መራጮች ቁጥር 2.3 ሚሊዮን መኾኑንም ገልጿል።
በምርጫው ምክንያት ነገ ሲዳማ ዞን ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት ዝግ ይኾናሉ ተብሏል።
በዕለቱ ጫት መሸጥ፣ የድጋፍም ኾነ የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ መከልከሉ ተሰምቷል። (ኢዛ)



