ነፃነት አስፋው አረፉ
ወይዘሮ ነፃነት አስፋው
ከሕወሓት ነባር ታጋዮች አንዷ ነበሩ
ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ ከሕወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዷ የነበሩትና በተለያዩ መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ወ/ሮ ነፃነት ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ከዚህ ዓለም ዛሬ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ማረፋቸው ተነግሯል።
ወይዘሮ ነፃነት በመንግሥት የሥራ ኃላፊነታቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመኾንና በሌሎች ኃላፊነቶች ላይ ሠርተዋል።
በተለይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ በመኾን መሥራታቸው ይታወሳል።
የኢጋድ (ምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት) የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር ኾነው መሥራታቸውም ይጠቀስላቸዋል። (ኢዛ)



