ለፀረ-ሙስና አዲስ ኮሚሽነር ተሾመ
የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ የተሾሙት አቶ ጸጋ አራጌ
ሹመቱን የተሠጣቸው አቶ ጸጋ አራጌ ናቸው
ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 12, 2020)፦ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ጸጋ አራጌ ሹመት፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።
ዛሬ መጋቢት 3 ቀን የተሰበሰበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው አቶ ጸጋ አራጌ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ አማካሪ ኾነው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን፤ የሰሜን ወሎን በአስተዳዳሪነት፤ የአዴፓ የአዲስ አበባ አስተዳደር ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ኾነው ከማገልገላቸውም በላይ፤ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩ ናቸው።
የኮሚሽነሩ ሹመት የጸደቀው በ6 ድምፀ ተአቅቦ፣ በ11 ተቃውሞና በአብላጫ ድምፅ ነው። ሹመቱን ምክር ቤቱ እንዲያጸቅ የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው። (ኢዛ)



