የትግራይ ትወላጅ የአዲስ አበባ ብልጽግና አመራሮች

የትግራይ ትወላጅ የአዲስ አበባ ብልጽግና አመራሮች መግለጫውን በሰጡበት ወቅት

ድርጊቱ ፍጹም ሕገወጥና የአገሪቱን ሕግጋቶች መናድ ስለኾነ፤ ሕወሓት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳሰቡ

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 21, 2020)፦ የትግራይ ተወላጅ የኾኑ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሕወሓት በክልል ደረጃ ምርጫ አካሒዳለሁ ብሎ መነሳቱ ፍጹም ሕገወጥና የአገሪቱን ሕግጋቶች መናድ እንደኾነ በመግለጽ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳሰቡ።

የትግራይ ተወላጅ የኾኑት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ይህንን የገለጹት ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ያካሔዱትን ውይይት ካጠናቀቁ በኋላ ባወጡት የአቋም መግለጫ ነው። አምስት ዋና ዋና ነጥቦችን የያዘው የአመራሮቹ የአቋም መግለጫ ውስጥ በክልል ደረጃ ሕወሓት አደርገዋልሁ ያለውን ምርጫ የሚያወግዝ ነው።

ከዚህም ሌላ የምርጫውን መራዘም አስፈላጊነት በጠቀሰበት በዚህ መግለጫ በዚህ ወቅት ምርጫው ካልተደረገ በሚል ሕወሓት የያዘውን አቋም ለሕዝቡ ደኅንነት ደንታ የሌለው መኾኑን ያሳያልም ይላል። ሙሉን መግለጫ አስነብበኝ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!