የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት “ለሚ ኩራ”ን አሥራ አንደኛው ክፍለ ከተማ ያደረጉበት ስብሰባ

“ለሚ ኩራ” አሥራ አንደኛው ክፍለ ከተማ ኾኗል

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 20, 2020)፦ አዲስ አበባ ከተማ በአሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች ኖሯት እንድትዋቀር፤ ከቦሌና ከየካ ክፍለ ከተሞች በመክፈል አዲስ ክፍለ ከተማ ተዋቀረ።

በዛሬው ዕለት (ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም.) አዲስ አበባ ክፍለ ከተሞችን ቁጥር በአንድ ያሳደገውን ውሳኔ ያስተላለፈው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ነው። ምክር ቤቱ አሥራ አንደኛ ክፍለ ከተማ በማድረግ ያጸደቀው “ለሚ ኩራ” የሚል መጠሪያ ያለው ነው።

ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ በማቅረብ አዋጁን ያጸደቀ ሲሆን፤ “ለሚ ኩራ” የሚል መጠሪያ ያለው ይኸው አዲሱ ክፍለ ከተማ የተፈጠረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለ ከተሞችን በመክፈል የተቀየረ መኾኑ ተገልጿል።

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን አዳጊ የኾነውን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እና የማስተዳደር አቅምን ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ ስለመኾኑ ተጠቅሷል። ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠትም ይህ አደረጃጀት አስፈላጊ ነው ተብሎ ለምክር ቤቱ በማቅረብ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ሊጸድቅ ችሏል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ