በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ጁንታውን በመቃወም ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሔዱ ሰልፎች

በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ጁንታውን በመቃወም ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሔዱ ሰልፎች

መንግሥት ሕግ የማስከበሩን ሥራ አጠንክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ ተሰጠ

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 12, 2020)፦ የሕወሓት ጽንፈኛ ቡድን በቅርቡ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚቃወሙ ሰልፎች ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በተለያዩ የክልል ከተሞች ተካሒደዋል።

የጁንታውን ቡድን ክህደትና ጥቃት የሚያወግዙ መልእክቶችን በመያዝና በማሰማት የተቃውሞ ሰልፎች የተካሔዱት በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር ክልሎች የተለያዩ ከተሞች ነው።

መንግሥት በጁንታው ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃዎች ጭምር የሚደገፍ መኾኑ በተገለጸባቸው በእነዚህ ሰልፎች ላይ፤ መንግሥት ሕግ የማስከበሩን ሥራ አጠንክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ የተሰጠባቸውም ጭምር ነበሩ።

ለመከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ፤ ብሎም ከሠራዊቱ ጎን በመኾን አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉም በየአካባቢው የተደረጉት ሰልፎች ላይ ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ