"ጂ-20" (G-20) በመባል የሚታወቁት ሀገራት አፕሪል 2 ቀን 2009 እ.ኤ.አ. (ኀሙስ መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም.) ሎንዶን ላይ ባደረጉት ስብሰባ የተገኙትን የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በመውጣጣት ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተደምጧል።

 

ይህንን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኀኖች ልዩ ትኩረት ሰጥተው አስተላልፈውታል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከኢትዮጵያውያን ሌላ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም ተገኝተዋል። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን "ሌባ!" ብለዋቸዋል።

 

ይህንን የተቃውሞ ሰልፍ በቪዲዮ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ! ከዚህም ሌላ የሎንዶኑን የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ ዓባይ ሚዲያ ድረ ገጽ በፎቶግራፍ የተደገፈ ሰፋ ያለ ዘገባ አቅርቧል። የዓባይ ሚዲያን ሰፊ ዘገባ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ