በምንም ምክንያት ርችት መተኮስ ተከለከለ
በአዲስ አበባ ርችት መተኮስ ተከለከለ
ርችት የሚተኮስ ግለሰብም ኾነ ተቋም በሕግ ይጠየቃል
ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 14, 2020)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ በምንም ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ርችት እንዳይተኮስና ርችት የተኮሰ ግለሰብም ኾነ ተቋም በሕግ የሚጠየቅ መኾኑን አስታወቀ።
ኮምሽኑ ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው ማሳሰቢያ፤ በአሁኑ ወቅት አገራችን ካለችበት የጸጥታ ሁኔታ በምንም ዐይነት ምክንያት ርችት መተኮስ የተከለከለ መኾኑን ገልጿል።
ይህንን መልእክት በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በሕግ የሚጠየቅ መኾኑንም አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ምክንያት በማድረግ ርችት እየተኮሱ በመኾኑና አሁን ካለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻር ርችት መተኮስ መከልከሉን ገልጿል። (ኢዛ)



