PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየሔደ ነው አሉ

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 15, 2020)፦ በትግራይ ክልል የሚካሔደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ በጥሩ ሁኔት እየተካሔደ መኾኑንና ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ የሕግ ማስከበር ሥራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ መኾኑን ከመግለጻቸውም ባሻገር፤ “ፍትሕ ታሸንፋለች፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ የሐሰተኛው አጥፊ ቡድን መጨረሻ ተቃርቧል”ም ብለዋል።

“የሕግ የበላይነትን በማስከበር ደግሞም አገራችንን በመዝረፍና ሰላሟን በማወክ የተሰማሩትን ተጠያቂ በማድረግ፤ ዘላቂ ሰላም እና ኁባሬ የሚኾን ጠንካራ መሠረት እንገነባለን” ያሉት ዶ/ር ዐቢይ፤ በተለይም ባላፉት ቀናት የታዩት ሁኔታዎች በሕወሓት ውስጥ ያለውን አጥፊ ቡድን ትክክለኛ ማንነት የገለጡ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።

በሰብአዊነት እና በሰላም ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉ ተጥያቂዎች እንደሚኾኑ በማመልከት፤ ፍትሕ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ባለን ውሳኔ በቆራጥነት እንገሰግሳለን ብለዋል።

የመልእክታቸው ማሳረጊያም “በሴቶች እና በወንዶች ልጆችዋ ጽናት እና ቆራጥነት ኢትዮጵያ ብቻዋን የሕግ የበላይነት የማስከበሩን ዘመቻ በብቃት ታጠናቅቃለች” የሚል ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ