ወልቃይት ጠገዴ

ወልቃይት ጠገዴ

በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሰፈራ ጣቢያን ለማጥፋት ዓላማ ሊውል ነበር

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 22, 2020)፦ ከቀድሞ የሕወሓት ታጋዮች በርካታ መጠን ያላቸው የጦር መሣሪያዎችን በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሰፈራ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ። የተያዙት መሣሪያዎች ዲቪዥን የሰፈራ ጣቢያን ለማጥፋት ዓላማ ሊውል ነበር።

ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረውን ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር የዋለው በመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ በጥምረት በተካሔደ ግዳጅ መኾኑን የሰሜን ዕዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ጄኔራል ሙሏአለም አድማሱ ገልጸዋል።

ከቀድሞ የሕወሓት ታጋዮች እጅ የተገኘው ይህ የጦር መሣሪያ፤ በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሰፈራ ጣቢያ መኾኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከተያዙት የጦር መሣሪያዎች ውስጥ 207 ክላሾችና 9,080 ጥይቶች ይገኙባቸዋል።

የተለያዩ ማካሮቭ ሽጉጦች፣ 26 አርባ ጎራሽ እና 18 አስር ጎራሽ የተባሉ የጦር መሣሪያዎችና ቦምቦችም በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የጦር መሣሪያዎች ውስጥ ተካትተዋል። ሌሎች ተያያዥ መሣሪያዎችና መረጃዎችም ተይዘዋል።

በመረጃው መሠረት ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች እና ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዲሰፍሩ ሲደረግበት በቆየው የመኖሪያ ጣቢያ የተገኘውን የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ያለምንም የተኩስ ልውውጥ፤ በልዩ ወታደራዊ ጠበት የተከናወነ መኾኑን ጄኔራል ሙሉዓለም አድማሱ አስረድተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ