ተጠባቂው የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ነገ ይጀመራል

ብልጽግና ፓርቲ
አጀንዳው ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ነው
ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 3, 2020)፦ በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ የሚጠበቀው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ነገ ዓርብ ኅዳር 25 ቀን ዓ.ም. ይጀምራል።
ፓርቲው ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ይህ ስብሰባ ከወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መወያየትና በቀጣይ ሒደቶች ላይ አቅጣጫ የሚያስቀምጥበት ነው። (ኢዛ)