ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የተጫኑ 207 ፈንጂዎች ተያዙ
ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ የነበሩትና በወልዲያ ጉምሩክ ኬላ የተያዙት 207 ፈንጂዎች
አሽከርካሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል
ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 17, 2021)፦ መዳረሻውን አዲስ አበባ ያደረገና ከመቀሌ የተጫኑ 207 ፈንጂዎች በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ወልዲያ በሚገኝ ጉምሩክ ኬላ ላይ ተያዘ።
እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ፈንጂዎችን የያዙ 23 ካርቶኖች የተያዙት በወልዲያ ጉምሩክ ኬላ ላይ እንደኾነ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳመለከተው፤ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ፈንጂዎቹን ጭኖ ሲጓጓዝ የነበረው አሽከርካሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል። (ኢዛ)



