አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ እና ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ እና ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንቷ ለትግራይና ለመተከል ተረጅዎች 50 ሺሕ ብር ሰጡ

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 1, 2021)፦ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በትግራይና በመተከል ዞን ለተጐዱ ወገኖች የሚል የ50 ሺሕ ብር እርዳታ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።

ፕሬዝዳንቷ ይህንን ድጋፍ ያበረከቱት “ሰብአዊነትና ፍቅር ለትግራይና ለመተከል” በሚል እየተንቀሳቀሰ ባለው የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በኩል ነው።

በአርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ የሚመራው ይህ ኮሚቴ፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዚህ የእርዳታ ማሰባሰብ መርኀ ግብር እስከ ትላንት ድረስ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል።

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የ50 ሺሕ ብር ድጋፉን ከማድረጋቸውም ሌላ የኮሚቴውን ሊቀመንበር ታማኝ በየነንም በቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ