የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

መራዘሙ የማይመለከታቸው አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ኦሮሚያ፣ ሐረሪ፣ ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ናቸው

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 5, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሁለተኛው ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ መራዘሙን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

እንደ ቦርዱ መግለጫ፤ የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልሎች በመርኀ ግብሩ መሠረት የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ሊጠናቀቅ እንደሚገባው አስታውሶ፤ በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች እክሎችን፣ እንዲሁም የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ እንዲራዘም ተደርጓል።

የሁለተኛው ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የተራዘመላቸው የአማራ፣ የሶማሌ፣ የአፋር፣ በኦሮሚያ የምዕራብና የምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና የሲዳማ ክልሎች ናቸው።

ቦርዱ ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁም ያሳሰበ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልሎች ወይም የከተማ መስተዳድሮች ማለትም አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ኦሮሚያ፣ ሐረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁን ቦርዱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ