National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አቶ ሁሴን አባቴ እና አቶ አስቻለው ባቡ ከየካቲት 26 ቀን ጀምሮ ታስረው ነበር

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 17, 2021)፦ በደቡብ ክልል በዘንድሮው ምርጫ 2013 ለመወዳደር የተመዘገቡ በደቡብ ክልል ፖሊስ በእስር ላይ የነበሩ ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች ከእስር መለቀቃቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን ግለሰቦቹ በደቡብ ክልል በሁለት የምርጫ ክልሎች የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በመኾን የተመዘገቡ በመኾኑ መታሰራቸው ሕጋዊ አለመኾኑን ለክልሉ ፖሊስ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባሰፈረው አጭር መልእክት፤ ታስረው የነበሩት ሁለት እጩ ተወዳዳሪዎች በትናንትናው ዕለት ተለቀዋል ብሏል።

በመስቃን እና ማረቆ ቁጥር ሁለት ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በመኾን የተመዘገቡትና በፖሊስ ታስረው የቆዩትን አቶ ሁሴን አባቴ እና አቶ አስቻለው ባቡ ከየካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መታሰራቸውን አሳውቆም፤ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በቀር መታሰር እንደማይቻሉ ምርጫ ቦርድ በመግለጽ እንዲፈቱ በደብዳቤ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል። የክልሉ ፖሊስም እጩ ተወዳዳሪዎቹን ከእስር የፈታው፤ ቦርዱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እንደኾነም ታምኗል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ