National Electoral Board of Ethiopia (NEBE)

ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ካገኙት ፓርቲዎች መካከል የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) ሰርቲፊኬት

ምርጫ ቦርድ የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የሌሎች ፓርቲዎች የእውቅና ጥያቄን እየተመለከተ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 11, 2019)፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእውቅና ሰርቲፊኬት (የምሥክር ወረቀት) መሥጠቱን ቀጥሏል። ዛሬ ለዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መሥጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በዛሬው ዕለትም (ታኅሣሥ 1 ቀን 2012 ዓ.ም.) ለዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእውቅና ሰርቲፊኬት የሠጣቸው ፓርቲዎች የአፋር ሕዝባዊ ፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኦሕፍዴፓ)፣ የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ (ኦሕነፓ)፣ ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)፣ ምቹ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ)፣ ቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ)፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)፣ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)፣ ወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ወብን) እና ሱማሌ አንድነት ፓርቲ (ሱአፓ) ናቸው።

እነዚህ ፓርቲዎች በምዝገባ ሒደት ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ዛሬ ታኅሣሥ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. እውቀና እንደሠጣቸው ቦርዱ በይፋ አስታውቋል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መንገድ እውቅና የሠጣቸውን ፓርቲዎች እያስተዋወቀ እንደሆነ ይታወቃል።

በአሁኑ ወቅትም የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የሌሎች ፓርቲዎች የእውቅና ጥያቄን እየተመለከተ እንደኾነ ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ