PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

በአግባቡ የሚሠሩትን ደግሞ መሸለም ይገባል አሉ

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 21, 2021)፦ በየትኛውም የሕግ ማስከበር ተግባር የመከላከያ ሠራዊታችንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፤ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፤ ዛሬ ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ስብሰባ ማድረጋቸውን ገልጸው፤ በዚህ ስብሰባ ላይ በየትኛውም ሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊቱንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን አመልክተዋል።

በአንጻሩም በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የተጠያቂነት እና የሥነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ሥርዓት እርምጃ የሚወስድባቸው ይኾናል” ብለዋል።

ሠራዊታችን የሰላም ጠባቂ እና የአገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር በመኾኑ፤ የሚሰማቸውን ኩራት የገለጹ መኾኑንም በዚሁ የፌስቡክ ገጻቸው አመልክተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ