ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ለፓርላማው ማብራሪያ ይሰጣሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ
ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 22, 2021)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጡበታል የተባለው መደበኛ ስብሰባውን ያካሔዳል።
በነገው ስብሰባ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡበት ስለመኾኑም ታውቋል። (ኢዛ)



