ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ነበር የተባለ 180 ሽጉጥና ከ2,800 በላይ ጥይቶች ተያዙ
በቁጥጥር ሥር የዋሉት 180 ሽጉጦች እና ከ2,800 በላይ ተተኳሽ ጥይቶች
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርምራ እየተደረገባቸው ነው
ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 14, 2021)፦ ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ 180 ሽጉጥ እና ከ2,800 በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ለማጓጓዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎችን በማንኩሳ ከተማ መያዛቸው ተገለጸ።
የምዕራብ ጐጃም ዞን ፖሊስ መመሪያ እንዳስታወቀው፤ እነዚህን በሕገወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረው የጦር መሣሪያዎች መዳረሻቸው አዲስ አበባ ነበር።
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደኾነ ታውቋል። (ኢዛ)



