Ethiopian Election 2021

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

በአንድ የምርጫ ጣቢያ መመዝገብም ኾነ መምረጥ የሚችለው ሰው ቁጥር 1,500 ብቻ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 19, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ተጨማሪ 28 ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎችን መክፈቱን አስታወቀ።

እነዚህን ንዑስ ጣቢያዎች የከፈተው፤ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች 1,500 ሰው መዝግበው መዝገባቸው ማለቁን ለቦርዱ ሪፖርት በመድረሱ እና በአንድ የምርጫ ጣቢያ 1,500 ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ መዝገቡ ስለሚዘጋ፤ ሌላ ዙር 1,500 መራጮች የሚመዘገቡት በአዲስ ንዑስ ጣቢያ በመኾኑ ነው።

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ተጨማሪ 28 ንዑስ ምርጫ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

እንዲህ ያለውን ተመሳሳይ ሒደት አስፈላጊ በኾነባቸው ቦታዎች ተጨማሪ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች ሊከፍት እንደሚችል ቦርዱ አክሎ ገልጿል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከምርጫ ቦርድ የተሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ የሚከተለው ነው። (ኢዛ)

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ

በአሁኑ ወቅት በ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ እንደኾነ ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች 1,500 ሰው መዝግበው መዝገባቸው ማለቁን ቦርዱ በሪፓርቱ ደርሶታል። በዚህም መሠረት ይህንን አጭር ማብራሪያ ያቀርባል።

1. በምርጫ አዋጁ 1162/2013 መሠረት አንድ ምርጫ ጣቢያ መመዝገብ የሚችለው 1,500 ሰው ብቻ ሲሆን፤ ይህም የኾነው በድምፅ መስጫ ቀን የሰው መጨናነቅን እና የዜጎች የመምረጥ መብትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

2. አንድ የምርጫ ጣቢያ 1,500 ሰው ሲሞላ የሚከተሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ

- አስፈጻሚዎች በተመሳሳይ ምርጫ ክልል እና በቅርብ ርቀት ያሉ የምርጫ ጣቢያዎችን በማጣራት መራጮች ካርድ የሚያገኙበትን ቦታ ይጠቁማሉ።

- የምርጫ ጣቢያው 1,500 ሰው ከመዘገበ በኋላ መዝገቡን የሚዘጋ ሲሆን፤ ሌላ ዙር 1,500 መራጮች የሚመዘገቡት በአዲስ ንዑስ ምርጫ ጣቢያ ይኾናል። ይህንንም ለማድረግ ተጨማሪ ቁሳቁስ የምርጫ ጣቢያ ኮድ እና የምርጫ አስፈጻሚችን ምደባ የሚጠይቅ ሲሆን፤ ከድምፅ መስጫ ቀን በፊት ደግሞ ተጨማሪ ቢሮዎችን ማዘጋጀት የሚጠይቅ ይኾናል።

በዚህም መሠረት፤ ቦርዱ በዛሬው ዕለት አዲስ ንዑስ ጣቢያዎችን በመክፈት ቁሳቁስ ያሰራጨ ሲሆን፤ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተለመደ ትብብራቸውን በመስጠት ተጨማሪ ቢሮዎችን ለመክፈት ቦርዱን እንዲተባበሩት ይጠይቃል።

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተጨማሪ የንዑስ ምርጫ ጣቢያ ተከፈተባቸው ቦታዎች፤
1. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 9_1 ንዑስ ጣቢያ
2. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 4 ንዑስ ጣቢያ
3. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 2 ንዑስ ጣቢያ
4. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 14 ንዑስ ጣቢያ
5. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 17 ንዑስ ጣቢያ
6. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ አባይ ንዑስ ጣቢያ
7. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ ካ.ቁ 4 ንዑስ ጣቢያ
8. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ ካ- ቁ.3 ንዑስ ጣቢያ
9. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ አባዶ -1 ንዑስ ጣቢያ
10. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ አያት ንዑስ ጣቢያ
11. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ ጣፎ -2 ንዑስ ጣቢያ
12. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ አያት ንዑስ ጣቢያ
13. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ ገብርኤል ቁ.1 ንዑስ ጣቢያ
14. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ መሪ 2ለ1 ንዑስ ጣቢያ
15. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ መሪ 1ሀ ንዑስ ጣቢያ

በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ የተከፈቱ ንዑስ ምርጫ ጣቢያዎች

1. አቦምሳ-02 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-4 ንዑስ ጣቢያ
2. አቦምሳ 02 ቀበሌ አቦምሳ ቁጥር 1 ንዑስ ጣቢያ
3. አቦምሳ 02 ቀበሌ አቦምሳ ቁጥር 2 ንዑስ ጣቢያ
4. አቦምሳ -02 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-3 ንዑስ ጣቢያ
5. አቦምሳ -01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-1 ንዑስ ጣቢያ
6. አቦምሳ -01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-2 ንዑስ ጣቢያ
7. አቦምሳ-01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-3 ንዑስ ጣቢያ
8. በሌ 01 ምርጫ ጣቢያ በሌ 01 -ሀ ንዑስ ጣቢያ
9. በሌ 01 ምርጫ ጣቢያ በሌ 01 -ለ ንዑስ ጣቢያ
10. እተያ ምርጫ ጣቢያ እተያ ንዑስ ጣቢያ
11. ሲርማ ምርጫ ጣቢያ ሲርማ 1 ""ሀ"" ንዑስ ጣቢያ
12. መልካ አማና ምርጫ ጣቢያ ለ ንዑስ ጣቢያ
13. መና-02 ምርጫ ጣቢያ 02-ለ ንዑስ ጣቢያ

ሲሆኑ በተጨማሪ ይህንኑ ተመሳሳይ ሒደት በመከተል አስፈላጊ በኾኑ ቦታዎች ሁሉ ተጨማሪ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎችን እንደሚከፍት ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ