ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ከአምባሳደር ጊታ ፓሲ

ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ በአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ መኖሪያ ቤት ከአምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በተገናኙበት ወቅት

ሰሞኑን በቪዲዮ ያስተላለፉት መልእክት እና የትግራይ ሰብአዊ ቀውስ ዋነኛ አጀንዳቸው ነበር

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 10, 2021)፦ የአሜሪካዋ አምባሳደር ጊታ ፓሲ፤ ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓርትሪያክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን በአምባሳደርዋ መኖሪያ ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተሰማ።

በብፁዕነታቸው እና በአምባሳደሯ መካከል የተደረገው ውይይት በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ እና በተለይም ደግሞ በትግራይ ክልል ካለው ሰብአዊ ቀውስ ጋር የተያያዘ መኾኑን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

የብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰሞኑን በቪዲዮ ያስተላለፉት መልእክት የመወያያው አጀንዳ እንደነበርም መረጃው ያመለክታል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ