የፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ ያበቃል
የምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ
አንዳንድ የአዲስ አበባ መንገዶች ዝግ ይኾናሉ
ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 16, 2021)፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013 ሲያካሒዱ የቆዩት ቅስቀሳ በዛሬው ዕለት (ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም.) የሚጠቃለል ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ አንዳንድ የአዲስ አበባ መንገዶች ለአገልግሎት ዝግ ይኾናሉ።
የከተማዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው በተለይ ከፒያሳ አራዳ ሕንጻ ወደ ደጎል አደባባይ፣ ከአራዳ ሕንጻ ወደ ምኒልክ አደባባይ፣ ከመዘጋጃ ቤት እስከ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እና መስቀል አደባባይ ዙሪያውን ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ለትራፊክ ዝግ ይኾናሉ። (ኢዛ)



